ይህ ጽሁፍ ረጅም ሰዓት ለሚያስተምሩና ለሚዘምሩ ወገኖች በድምጽ (በጉሮሮ) ላይ ተጽዕኖ ሊያመጣባቸው ይችላል በሚል ሊወገዱ የሚገባቸው መጠጦች ከብዙዎቹ በጥቂቱ እነዚህ ናቸው ተብሎ ይታሰባል
1. አረንጓዴ ሻይ (green tea ) – ይህ ድምጽ የሚፈጠርባቸው አካባቢዎችን የማድረቅና የመሰነጣተቅ ባህሪ ስላለውና በተፈጥሮ በተለያዩ የውስጥ ሰውነታችን ላይ ያለውን እርጥበት እንዲቀንስ ስለሚያደርግ እንዳይጠጣ ይመከራል::
2. ወተት (milk ) – ወተት በጉሮሮአችን እና በአፍንጫችን መንገድ ላይ ከፍተኛ የወፍራም ምራቅ ወይም (አክታ) ክምችትን ስለሚያስከትል ለድምጽ አወጣጥ ላይ ከፍተኛ ችግር ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል::
3. የበረዶ ውሃ (Ice cube/chips) – የቀዘቀዘ ውሃ እየጠጣን ማስተማርም ሆነ መስበክ ወይም መዘመር ለድምጽ መልካም ያልሆነበት በድምጽ መፈጠሪያ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች በቅዝቃዜ ስለሚኮማተሩና ድምጽ ለማውጣት ያለው ጫና እንዲሰነጣጠቁ ያደርጋቸዋልና የሞቀ ሻይ ቢጠጣ (preferably peppermint or licorice root tea; both are fabulous.) መልካም እንደሆነ ይመከራል
4. ጋዝ ያላቸው መጥጦች(ኮካ ፔፕሲ አምቦ ውሃ … ) እነዚህ መጠጦች በሆዳችን ውስጥ ጋዝ ማለትም አየር ይፈጥርና እየሰበክንም ይሁን እየዘመርን ከሆዳችን ውስጥ በከፍተኛ ግፊት ወደ ድምጽ ማውጫ ጉሮሮ ይመጣና በድምጽ አወጣጥ ላይ ችግር ይፈጥርብናል እንደገናም የሆዳችንን ጡንቻ ዘና አድርገን በዲያፍራም የሳምባ ጡንቻ ብቻ እየተነፈስን እንዳናስተመር/እንዳንሰብክ ወይም እንዳንዘምር ያደርጉናል::
ካሱ ቦስተን
እባክዎን ካነበቡ በኋላ ላይክ የሚለውን ይጫኑ እንዲሁም መልእክቱን ለሌሎች ያካፍሉ አመሰግናለሁ