ክፍል 2
ደቀመዝሙር ማለት ወደኋላ የማያይ ጌታውን ብቻ እየተከተለ ወደፊት የሚሄድ ነው። “ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም” ተብሎ ተፅፎአልና። ጌታ የሎጥን ሚስት አስቧት ያለን ለምን ይሆን? ከወጡ፣ ካመለጡ ፣ከዳኑ በኋል መጥፋት ስላለ አይደለምን? የሎጥ ሚስት ወደኋላ አልሄደችም ግን በልቧ ወደ ኋላ ሄደች። ጌታ አካላችን ያለበትን ሳይሆን ልባችን ላበትን ያያል፡ ደቀ መዝሙር የሚያደርገን፡- የልብ እምነት፣ የልብ መገረዝ፣ የልብ ውሳኔና ጭካኔ እንጂ በውጭ የምናሳየው ግብዝነት አይደለም። ጌታን ስንከጽሁፌ ላይ እንደገለጽኩት. በማለት ሃሳቤን አስፍሬ ነበር እንዴት ነው የምንቀንሰው የሚለውን እናያለን ጽሁፌ ላይ እንደገለጽኩት. በማለት ሃሳቤን አስፍሬ ነበር እንዴት ነው የምንቀንሰው የሚለውን እናያለን ተል በእግራችን ሳይሆን በልባችን እየተከተልነው መሆኑን ይመዝነናል።
በክፍል 1. ጽሁፌ ላይ እንደገለጽኩት ደቀመዝሙር ያልሆነውንና የኢየሱስ ወንጌል የማያረካውን ህዝብ ከአዳራሾቻችን መቀነስ አለብን በማለት ሃሳቤን አስፍሬ ነበር እንዴት ነው የምንቀንሰው የሚለውን እናያለን፦
ቤተ ክርስቲያን ህዝቡን በእውነተኛና ማመቻመች በሌለበት ንጹህ ቃል በመመገብ ምእመኑ እራሱን ክዶ መስቀሉን እየተሸከመ እንዲጓዝ የሚያደርግ ምግብ በመመገብ ነው፥ አለበለዚያ በየጊዜው ኮንፍራንስ እያዘጋጀንና የተመኙትን የሚሰብኩላቸውንና የሚተነብዩላቸውን እየጋበዝን ከቀጠልን ግን ለሚጠፋ መብል ኢየሱስን የሚከተል ብዙ ህዝብ እንደያዝን እንሰነብታለን።
ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በኢየሱስ ወንጌል መለኪያ ተለክተው ያላለፉትንና ወደ ኋላ የተመለሱትን ሰዎች ሰብስበው ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ተብለው መጠራታቸው ከኢየሱስ የተለየ ሌላ ወንጌል እየሰበኩ መሆናቸውን አጋልጦባቸዋል። ለመሆኑ እነዚያን በኢየሱስ መለኪያ ያላለፉትን ዛሬ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት የት አግኝተዋቸው ነው ደቀመዝሙር ያደረጓቸው? የሚል ካለ እነዚያን ኢየሱስ የመለሳቸውን ሰዎች አይነት ልብና አመለካከት ይዘው የመጡትን እነዚያን መቀበላቸው መሆኑ ሊገባን ይገባል። ይህን ስንል ብዙ ወንድሞችና እህቶች ያሏቸው አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሐሰትን ሰብከዋል ማለት ሳይሆን በዚህ መለኪያ ያላለፉ ብዙ ሰዎችን መሰብሰባቸውን መግለጻችን ነው። ምናልባት አንዳንዶቻችን ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ወደርሱ እንዲመጡ ይጠራ ነበር እንዲያውም “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” አላለም ወይ? እንል ይሆናል አዎ ብሎአል። የመጣውም ደካሞችን ኃጢአተኞችን ሊጠራና ሊያድን ነው። ይሁን እንጂ እነዚህ የተጠሩት ደካሞች ለመዳን በዚህ መለኪያ ማለፍ አለባቸው። ኢየሱስ እነዚህን ሁለቱን መልእክቶች መሳ ለመሳ አንዱን ከአንዱ ሳይለይ ነው ያወጀው። ሰው ሁሉ በርሱ እንዲያምንና እንዲከተለው እየተጣራ መለኪያን ግን እንደየሰው ፍላጎትና ቁጥር አልቀነሰም። ለተጠሩት ሁሉ መለኪያው አንድ ነው። አንድም ቀን ኢየሱስ ይህንን መለኪያ ዝቅ አላደረገም። ምክንያቱም ወደ ህይወት የሚወስደው መንገድ ጠባብ ነው። ህይወትን ሊያገኝ የወደደ ሁሉ በዚያ መንገድ ማለፍ አለበትና። ለዚህም ነው በዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን መለኪያ እንኳንስ ወደ ኋላ ተመለሱ ሊባሉ ይቅርና «መሪና አገልጋይ ተብለው ሊሾሙ የሚችሉ ሰዎችን ጌታ ኢየሱስ ግን «ለደቀ መዝሙርነት ብቁ አይደላችሁም» ብሎ የመለሰው። እስኪ ለምሳሌ የርሱን የደቀመዝሙርነት መለኪያ ያለፉትናና ወደኋላ የተመለሱትን ጥቂት ሰዎች እንመለከታለን፦ በክፍል 3 ይቀጥላል …
ካሱ ቦስተን
እባክዎን ካነበቡ በኋላ ላይክ የሚለውን ይጫኑ እንዲሁም መልእክቱን ለሌሎች ያካፍሉ አመሰግናለሁ